ተከታዩ አንቀፅ በወረደ ጊዜ: {ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።} ማለትም አላህ በናንተ ላይ ለዋለላችሁ ፀጋ ማመስገናችሁን የምትጠየቁ ናችሁ። ዙበይር ቢን አልዓዋም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ስለማንኛው ድሎት ነው የምንጠየቀው? እነዚህ ሁለት ፀጋዎች ለመጠየቅ የሚያነሳሱ አይደሉም'ኮ እነርሱም ተምርና ውሃ ናቸው።" ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "እናንተ በዚህ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ከመሆናችሁም ጋር ስለነዚህ ፀጋዎች ትጠየቃላችሁ። እነዚህ ሁለቱም ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎቹ መካከል ናቸውና።" አሉ።