ከዓዲይ ቢን ሓቲም እንደተላለፈው: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ "አይሁዶች ቁጣ የሰፈነባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳሳቱ ናቸው።" ሶሒሕ ነው። - ቲርሚዚ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አይሁዶች እውነትን እያወቁ ባለመተግበራቸው አላህ የተቆጣባቸው ህዝቦች እንደሆኑ ተናገሩ። ክርስቲያኖች ደግሞ ያለ ዕውቀት የሚሰሩ ስለሆኑ የተሳሳቱ ህዝቦች ናቸው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ዕውቀትና ተግባርን ሰብስቦ መሄድ ቁጣ ከሰፈነባቸውም ከተሳሳቱትም ሰዎች መንገድ መዳኛ መሆኑን እንረዳለን።
  • ከአይሁዶችና ክርስቲያኖች መንገድ መጠንቀቅና ቀጥተኛ የሆነውን የኢስላምን ጎዳና አጥብቀን መያዝ እንዳለብን እንረዳለን።
  • በመሰረቱ አይሁዶችም ክርስቲያኖችም የተሳሳቱና ቁጣ የሰፈነባቸው ህዝቦች ናቸው። ነገር ግን ልዩ መገለጫቸው የአይሁዶቹ ቁጣ የሰፈነባቸው መሆናቸው ሲሆን የክርስቲያኖች ልዩ መገለጫ ደግሞ መሳሳታቸው ነው።