ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "ማንኛውም ለወንድሙ ‹አንተ ከሀዲ› ያለ ሰው በርግጥም በርሷ (በከሀዲነቷ) ላይ አንዳቸው ወድቀዋል። እንዳለው ሆኖ ከሆነ (መልካም) ያለበለዚያ ወደርሱ ትመለሳለች።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።