ከአቡ ደርዳእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።" ሶሒሕ ነው። - አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን ከተግባሮችም ከንግግሮችም የአማኝን ሚዛን የሚደፋለት መልካም ስነ ምግባር መሆኑን ተናገሩ። ይህም ፊትን ፈታ በማድረግ፣ ሌላን ከመጉዳት በመቆጠብና መልካም ነገርን ለሌሎች በመለገስ ነው። የላቀው አላህ፤ በድርጊትም ይሁን በንግግር አፀያፊ የሆነንም በአንደበቱ ብልግና የሚናገርንም ሰው ይጠላል።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የመልካም ስነ ምግባርን ትሩፋት እንረዳለን። መልካም ስነምግባር ባለቤቱን የአላህን ውዴታና የባሮቹን ውዴታ እንዲያገኝ ያበቃዋል። እርሱ የትንሳኤ ቀን ከሚመዘኑትም እጅግ ትልቁ ነው።