ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለአሸጅ ዐብዲል ቀይስ እንዲህ አሉ: "አንተ ውስጥ ሁለት አላህ የሚወዳቸው ነገሮች አሉ። እነርሱም አስተዋይነትና መረጋጋት ናቸው።"» ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።