ነቢዩ ((የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ለጀነት ነዋሪዎች በውስጧ እያሉ እንዲህ እንደሚል ነገሩን: "የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!" እነርሱም "ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል" በማለት ለርሱ ይመልሳሉ። እርሱም ለነርሱ: ተደሰታችሁን? ይላቸዋል። እነርሱም: አዎን ተደስተናል። ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው? ይላሉ። አላህም: ከዚህ የተሻለ ነገር ልስጣችሁን? ይላቸዋል። እነርሱም: ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ነገር ምን አለና? ይላሉ። እርሱም: ዘውታሪ የሆነውን ውዴታዬን አሰፍንባችኋለሁ። ከዚህ በኋላ በናንተ ላይ መቼም አልቆጣም። ይላቸዋል።