ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዒድ ቀን ወደ መስገጃ ስፍራ ወጡ። ሴቶችን ለብቻቸው ሊገስጿቸው ቃል ገብተውላቸው ነበር። የዛን ቀን ቃላቸውን አሳኩ። እንዲህም አሏቸው: እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! ምህረት መጠየቅንም አብዙ! እነርሱ ከትላልቅ ወንጀል ማስማሪያዎች መካከል ናቸው። እኔ ወደ ሰማይ ባረግኩበት ምሽት አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ ተመልክቻችኋለሁና። ከነርሱ መካከል የሆነች አንድ አስተውሎት፣ ብስለትና እርጋታን የተላበሰች ሴትም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ ለምንድነው አብዛኛው የእሳት ነዋሪ የሆንነው?" አለች። እርሳቸውም አሉ: ለብዙ ምክንያቶች ነው: እርግማንና ስድብ ታበዛላችሁ፣ የባል ሐቅን ትክዳላችሁ። ቀጥለውም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሴቶችን "አይምሮና ዲን የጎደለባቸው ሆነው የአይምሮ፣ የአስተሳሰብ፣ የቆራጥነት ባለቤት የሆነና ጉዳዩን የሚወስን የሆነን ወንድ የሚያሸንፍ እንደናንተ አልተመለከትኩም።" ብለው ገለጿቸው። እርሷም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የአይምሮና ዲን መጉደል ምንድን ነው?" አለች። እርሳቸውም "የአይምሮ መጉደልማ የሁለት ሴት ምስክርነት የአንድ ወንድ ምስክርነት ጋር ይስተካከላል። ይህ የአይምሮ ጉድለታችሁ ነው። የዲናችሁ መጉደል ደግሞ ቀናቶችና ምሽቶችን በወር አበባ ምክንያት ሳትሰግድና ጾሟን ትታ እያፈጠረች በመቆየቷ መልካም ስራን ማጓደሏ ነው። ነገር ግን እነርሱ በዚህ ምክንያት አይወቀሱምም አይጠየቁምም። ምክንያቱም የሰው ልጅ ገንዘብ በመውደድ፣ በመቸኮል፣ በመሃይምነትና ከዚህም ውጪ ባሉ ነገሮች ላይ ሆኖ እንደተፈጠረው ሁሉ ይህም የሴቶች ተፈጥሯቸው ነውና። ይህን ያስገነዘቡትም በነርሱ ከመፈተን እንድንጠነቀቅ ነው።