ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ጀነት ውስጥ ዛፍ አለች። ረጅም ጊዜ የተቀለበችና ፈጣን የሆነችን ፈረስ ምርጥ ጋላቢ መቶ አመት ጋልቦ ይህቺን ዛፍ አያቋርጣትም።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።