የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ከባልደረቦቻቸው አንድ ጉዳይ ደረሳቸው። እርሱም እነርሱ ለርሳቸው ጥያቄ እያበዙ መሆናቸው ነው። የዛኔም ተቆጥተው ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ: "በኔ ላይ ጀነትና እሳት ቀረቡ። ዛሬ ጀነት ውስጥ ካየሁት መልካም ነገር የበለጠ መልካም ነገር አይቼ አላውቅም። ዛሬ እሳት ውስጥ ካየሁት መጥፎ ነገር የበለጠም መጥፎ ነገር አይቼ አላውቅም። እኔ ያየሁትን ብታዩ፣ ዛሬና ከዛሬ በፊት ከተመለከትኩት ያወቅኩትንም ብታውቁ ኖሮ እጅግ ከፍተኛ ፍርሃትን ትፈሩ ነበር። ሳቃችሁ አንሶ ለቅሷችሁም ይበዛ ነበር።" አነስም ረዲየሏሁ ዓንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አለ: "በአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሓቦች ላይ ከዚህ ቀን የበለጠ ከባድ ቀን መጥቶ አያውቅም። ጭንቅላታቸውን ሸፍነው እጅግ ከማልቀሳቸው የተነሳ ለቅሷቸው ከአፍንጫ የሚወጣ የመንሰቅሰቅ ድምፅ ነበረው።" ዑመርም ረዲየሏሁ ዓንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ተነስተው እንዲህ አሉ: "በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነትና በሙሐመድ ነቢይነት ወደድን።" አነስ እንዲህ አለ: ያ ሰውዬም ተነሳና እንዲህ አለ: "አባቴ ማን ነው?" እርሳቸውም "አባትህ እከሌ ነው።" አሉ። በዚህን ጊዜም ይህቺ አንቀፅ ወረደች: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለፁ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ።} [አልማኢዳህ:101]