ለኡሳማ ቢን ዘይድ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ተባሉ: ዑሥማን ቢን ዐፋን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘንድ ገብተህ በሰዎች መካከል ስለተከሰተው ፈተናና ከመሰረቱ ፈተናውን በማጥፋት ላይ እንዲለፋ አታናግራቸውምን? እርሱም: ፈተናን ላለማባባስ ማስተካከልን በመፈለግ በድብቅ እንዳናገረው፤ መሪዎችን በይፋ ማውገዝንና በኸሊፋው ላይ የመንጠራራት ሰበብ መሆን እንደማይፈልግ ነገራቸው። ይህን ማድረግ የፈተናና የመጥፎ በር በመሆኑ ለዚህ በር የመጀመሪያው ከፋች መሆን እንደማይፈልግም ነገራቸው። ቀጥሎ ኡሳማ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - : እርሱ መሪዎችን በድብቅ እንደሚመክርና ከየትኛውም መሪ ጋር ቢሆን እንኳ እንደማይቅለሰለስና በፊትለፊታቸውም ጥፋታቸውን እንደማያሞግሳቸው ተናገረ። ይህንንም የሚያደርገው ይህንን ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰማ በኋላ ነው:- የትንሳኤ ቀን አንድ ሰው ተይዞ ይመጣና እሳት ውስጥ ይጣላል። ከቅጣቱ ሀይለኝነትና ከሀሩሩ አደገኝነት የተነሳም አንጀቱ ከሆዱ በፍጥነት ወጥቶ ይዘረገፋል። በዚህም ሁኔታ አህያ በወፍጮው (የድንጋይ መፍጫ) ዙሪያ እየዞረ እንደሚኖረው እሳት ውስጥ አንጀቱን ይዞ ይሽከረከራል። በዙሪያውም የእሳት ሰዎች በመክበብ ይሰበሰቡና "እከሌ ሆይ! በመልካም የምታዘን ከመጥፎ የምትከለክለን አልነበርክምን?" በማለት ይጠይቁታል። እርሱም: እኔ በመልካም የማዝና የማልፈፅመው ከመጥፎ የምከለክልና የምሰራው ሰው ነበርኩ ይላል።