ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ማለቱን ተናገሩ: "ደጋግ ባሪያዎቼን ጀነት ውስጥ ለማላቅ ስለርሱ ምንነት አይን ያላየችውን፤ ስለርሱ ባህሪ ጆሮ ያልሰማችውን፤ ስለእውነተኛ ሁኔታዋ በሰው ቀልብ ላይ ውል ብሎ ያላለፈና ያልተከሰተን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።" አቡ ሁረይራም (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: "ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ: {ይሰሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለነርሱ የተደበቀላቸውን (ፀጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።}" [አስሰጅዳ:17]