ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትንሳኤ ቀን እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት የሚቀጣው የእሳት ነዋሪ ለርሱ ሁለት የእሳት ጫማዎችና ማሰሪያዎች የሚደረግለት ሰው እንደሆነና ከአቃጣይነታቸው የተነሳ የነሃስ ድስጥ እንደሚንፈቀፈቀው አንጎሉም የሚንፈቀፈቅ መሆኑን፤ ከርሱ የበለጠ የሚቀጣ አንድም ሰው አለ ብሎም እንደማያስብ፤ እርሱ ግን እጅግ ዝቅተኛውን ቅጣት የሚቀጣ ነው መሆኑን ተናገሩ። ይህንን የሚያስበውም አካላዊ ቅጣቱ ከመንፈሳዊ ቅጣቱ ጋር በጋራ እንዲቀጣበት ነው።