explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጀሀነም ክልክልን በመዳፈርና ግዴታን ባለመወጣት የመሰሉ ነፍስያ በምትፈልጋቸው ነገሮች መሸፈኗን መከበቧን ገለፁ። በመሆኑም የነፍስያውን ፍላጎት በዚህ ረገድ የተከተለ ለጀሀነም ተገባ። ጀነት ደግሞ ትእዛዝ ላይ በመዘውተር፣ ክልከላን በመተውና በዚሁ ላይ ትዕግስት በማድረግ በመሰሉ ነፍስያ በምትጠላቸው ነገሮች መሸፈኗንና መከበቧን አብራሩ። ስለዚህም በዚህ ረገድ በቁርጠኝነት ነፍስያውን የታገለ ለጀነት የተገባ ሆነ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በስሜት ላይ ለመውደቅ ሰበብ ከሚሆኑ መሰናክሎች መካከል አስቀያሚና የተወገዘ የሆነውን ነገር ነፍስያ ወዳው እስክትዘነበልለት ድረስ ሸይጧን ማስዋቡ አንዱ ነው።
  • ወደ ጀሀነም እሳት መዳረሻ ከመሆናቸው አንፃር ከተከለከሉ ፍላጎቶች መራቅና ወደ ጀነት የሚያደርሱ ከመሆናቸው አንፃርም የምንጠላቸው ነገሮች ላይ በመታገስ መታዘዛችንን እንረዳለን።
  • ነፍስያን መታገል፣ በዒባዳ ላይም መትጋት፣ በአምልኮ ዙርያ ያሉ የምንጠላቸውና የሚያስቸግሩን ነገሮች ላይም መታገስ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።