ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የዱንያ እሳት ከሰባ የጀሀነም እሳት ክፍል አንዷ ክፍል መሆኗን ተናገሩ። የአኺራ እሳት ከዱንያ እሳት በስልሳ ዘጠኝ እጥፍ የማቃጠል ደረጃዋ ይበልጣል። እያንዳንዱ የጀሀነም ክፍል ከዱንያ እሳት አቃጣይነት ጋር እኩል ነው። "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጀሀነም ውስጥ የሚገቡን ለመቅጣት የዱንያ እሳት’እኮ በቂ ነበረች።" ተባሉ። እርሳቸውም "የጀሀነም እሳት ከዱንያ እሳት በስልሳ ዘጠኝ ክፍል እንድትበልጥ ተደርጓል። የእያንዳንዱ ክፍል ሀሩርነት (የማቃጠል) ኃይልም እንደ ዱንያ እሳት አምሳያ ነው።" አሉ።