explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በአሏህ ላይ አንዳችም ሳያጋራ የሞተ በተወሰነ ወንጀሉ ተቀጥቶም ቢሆን መመለሻው ወደ ጀነት መሆኑን፤ በአሏህ ላይ አንዳችም አጋርቶ የሞተ ደግሞ ጀሀነም መዘውተሪያው መሆኑን ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ተውሒድ ያለው ትሩፋት፤ በእሳት ውስጥ ከመዘውተር ለመዳንም ሰበብ መሆኑን፤
  • የሰው ልጅ ከጀሀነምም ይሁን ከጀነት ጋር ያለው ቅርበት፤ በእነርሱና በሰውየው መካከል ያለውም ሞት ብቻ መሆኑን፤
  • ከጥቂትም ይሁን ከብዙ ሽርክ መጠንቀቅ እንደሚገባ፤ ምክንያቱም ከጀሀነም እሳት መዳን የሚቻለው ያንን በመራቅ ስለሆነ፤
  • ስራዎች ዋጋ የሚሰጣቸው በፍፃሜያቸው መሆኑን እንረዳለን።