explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም እነርሱን በሚገባ ከጠበቀ ጀነት የሚገባባቸው የሆኑ ሁለት ጉዳዮችን ተናገሩ። የመጀመርያው፡ የላቀው አሏህን ከሚያስቆጣ ንግግር ምላስን መቆጠብ፤ ሁለተኛው፡ ብልትን ብልግና ከመፈፀም መጠበቅ ነው። ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ወንጀል የሚፈፀምባቸው እነዚህ ሁለቱ አካላት ስለሆኑ ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ምላስንና ብልትን መጠበቅ ጀነት ለመግባት ሰበብ መሆኑን እንረዳላን።
  • ምላስና ብልት ተለይተው የተጠቀሱበት ምክንያት የሰው ልጅ በዱንያውም ሆነ በአኺራው ለሚመጣበት መከራ ዋነኛ ምንጮች ሁለቱ በመሆናቸው ነው።