ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን የምንጫቸው መጠጫ እቃ ከሰማይ ኮኮቦች ቁጥር እንደሚበዛ ማሉ። ይህ የሰማይ ከዋክብት ቁጥርም ጨረቃ በሌለበት ድቅድቅ ምሽት ወቅት ግልፅ ይሆናል። ምክንያቱም ጨረቃ ባበራችበት ምሽት ኮኮቦች በጨረቃዋ ብርሃን ስለሚሸፈኑ ግልፅ አይሆኑም። እንዲሁም ደመና በሌለበትም ምሽት ወቅት ነው። ምክንያቱም የደመና መኖር ኮኮቦችን ከመታየት ይከለክላል። ከጀነት እቃ ውስጥ መጠጥን የጠጣ መቼም አይጠማም። ይህም አንድ ጠጪን የሚያጋጥመው የመጨረሻ ጥም ይሆናል። ከጀነት ሁለት አሸንዳዎች ወደ ኩሬያቸው ይፈሳል። የምንጫቸው አግድመቱ የእርዝማኔው አምሳያ ነው። የኩሬያቸው ማእዘናት እኩኩል ነው። እርዝማኔው ከዐማን (ሻም ውስጥ የምትገኝ በልቃእ የምትባል ሀገር ናት።) እስከ አይለህ (በሻም ጫፍ የምትገኝ የታወቀች ከተማ ናት።) የሚደርስ ርቀት ያክል ነው። የኩሬያቸው ውኃ ከወተት እጅግ የበዛ ንጣት ያለው ሲሆን ጣእሙም ከማር ጣእም ጥፍጥና የበለጠ እጅግ ጣፋጭ ነው።