ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት አዛን የሚያደርግን ሰው የሰማ ከ"ሐይየዐለተይን" ውጪ ከኋላው አስከትሎ (ሙአዚኑ) የሚለውን አምሳያ እንዲል ጠቆሙ። ከ"ሐይየዐለተይን" በኋላ ግን "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" ይላል። አዛኑ ከተጠናቀቀ በኋላም በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላትን ያወርዳል። እነሆ በርሳቸው ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶላት ያወርድበታልና። አላህ በባሪያው ላይ ሶላት አወረደ ማለት መላኢኮች ዘንድ ባሪያውን ማወደሱ ነው። ቀጥለውም አላህ ወሲላን ለሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲሰጣቸው እንድንጠይቅ አዘዙ። እርሷም በጀነት ውስጥ የምትገኝ ከፍተኛዋ ደረጃ ናት። ይህቺ ስፍራም ከሁሉም የአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ ለሌላ ለማንም አትሰጥም አትበጅምም (አትገባም)። ያ ባሪያ እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መልኩ የተናገሩት ለመተናነስ ብለው ነው እንጂ ይህቺ ከፍተኛ ደረጃ ለአንድ ባሪያ እንጂ ለማንም የማትሆን ከሆነች ያ አንድ ባሪያ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንጂ ማንም አይሆንም። እሳቸው ከፍጡራን ሁሉ በላጩ ፍጡር ናቸውና። ቀጥለው ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወሲላን ከአሏህ የለመነ ሰው የርሳቸውን ምልጃ እንደሚያገኝ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።