ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኢስራእና ሚዕራጅ ምሽት የአላህ ፍፁም ወዳጅ የሆኑትን ኢብራሂምን ዐለይሂ ሰላም እንዳገኙ ተናገሩ። ለርሳቸውም «ሙሐመድ ሆይ! ለኡመትክ የኔን ሰላምታ አድርስ! ጀነት አፈሯ ምርጥና ውሃዋም ጨውነት የሌለው ጣፋጭ ውሃ እንደሆነ፤ ጀነት ዛፍ የሌለበት ቀጥ ያለና ሰፊ ሜዳ ሲሆን የጀነት ተክልም ምርጥ ንግግሮችና ቀሪ የሆኑ መልካም ስራዎች እንደሆኑ እነርሱም: "ሱብሓነላህ" "ወልሐምዱሊላህ" "ወላኢላሃ ኢለሏህ" "ወሏሁ አክበር" እንደሆኑና አንድ ሙስሊም በደጋገማቸው ቁጥር ጀነት ውስጥ ተክል እንደሚተከልለት ንገራቸው።» አሉ።