ዑሥማን ቢን አቢልዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰይጣን በኔና በሶላቴ መካከል ጋሬጣ ሆነ በርሷ ውስጥ ከመመሰጥም ከለከለኝ። በኔ ላይ ሶላቴ ውስጥ የምቀራውን ቂረአቴን ቀላቀለብኝም አጠራጠረኝም።" የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት: "ይህ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ያገኘህና የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ። ወደ ግራህም ዞረህ ከትንሽ ምራቅ ጋር ሶስት ጊዜ ትፋ።" ዑሥማንም እንዲህ አለ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያዘዙኝን ነገር ፈፀምኩ። አላህም ከኔ ላይ አስወገደልኝ።"