ሰህል ቢን ሙዓዝ ቢን አነስ ከአባቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ምግብ በልቶ ‹አልሐምዱ ሊላሂለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒሂ ሚን ገይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላቁውዋህ› ያለ ሰው ያሳለፈው ወንጀል ለርሱ ይማርለታል።"» ትርጉሙም "ያለኔ ኃይልና ብልሃት ይህንን ላበላኝና ለለገሰኝ አላህ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው። ሐሰን ነው። - አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።