ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ንፋስን ከመሳደብና ከመርገም ከለከሉ። ምክንያቱም ንፋስ ከፈጣሪዋ የታዘዘች በመሆኗ እዝነትና ቅጣትን ይዛ ትመጣለች። እርሷን መስደብ ፈጣሪዋን አላህን መሳደብና በውሳኔው ማማረር ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከንፋሷ መልካም ነገር፣ ውስጧ ከያዘችው መልካም ነገርና ዝናብ ይዞ እንደመምጣት፣ ዘርን እንደማራባትና በመሳሰሉት የተላከችበትን መልካም ነገር አላህን በመጠየቅና ከንፋሷ ጉዳት፣ ውስጧ ከያዘችው ጉዳት፣ ቡቃያንና ዛፍን እንደ ማጥፋት፣ እንስሶችን ማጥፋት፣ ህንፃዎችን እንደማፍረስና ከመሳሰሉት ከተላከችበት ጎጂ ነገር በአላህ በመጠበቅ ወደ አላህ እንድንመለስ ጠቆሙ። አላህን ይህን መጠየቅ አምልኮን ለአላህ ማረጋገጣችንን ይጠቁማል።