ከኸውለህ ቢንት ሐኪም አስሱለሚየህ እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በአንድ ስፍራ ላይ አርፎ ከዚያም ‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ (ምሉዕ በሆኑ የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ጎጂ ነገሮች እጠበቃለሁ)› ያለ ሰው ከዛ ስፍራ እስኪንቀሳቀስ ድረስ አንዳችም አይጎዳውም።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰው ልጅ አንድ ስፍራ ላይ በሚያርፍበት ጊዜ የሚፈራቸውን ሁሉ አስፈሪ ነገሮች የሚከላከልበትን ጠቃሚ መጠበቂያና መጠጊያ ለኡመታቸው እየጠቆሙ ነው። ይህም ጉዞም ላይ ይሁን ሊዝናናም ይሁን ወይም ከዛ ውጪ ባረፈበት ስፍራ ላይ ከሚገኝ ፍጡራን ሁሉ ክፋት በትሩፋቱ፣ በበረከቱና በጥቅሙ የተሟላ በሆነውና ከሁሉም ነውርና ጉድለት የፀዳ በሆነው የአላህ ቃል ከተጠበቀና ከተጠጋ በዛ ስፍራ እስካለ ድረስ ከሁሉም ጎጂ ነገሮች ደህንነቱ ይጠበቃል።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በአላህ መጠበቅ አምልኮ ነው። የተፈቀደ የሚሆነውም በአላህ ወይም በስሞቹና በባህሪያቶቹ ሲጠበቅ ነው።
  • ከአላህ ባህሪያቶች መካከል አንዱ በሆነው የአላህ ቃል መጠበቅ እንደሚፈቀድ እንረዳለን። ይህም በማንኛውም ፍጡር ከመጠበቅ ተቃራኒ ሲሆን ከአላህ ውጪ ካለ አካል ጥበቃን መሻት ሺርክ ነው።
  • የዚህ ዱዓእ ትሩፋትና በረከትን እንረዳለን።
  • በዚክሮች መመሸግ (መከላከል) ሰውዬው ከክፋቶች እንዲጠበቅ አንዱ ሰበብ ነው።
  • በጋኔን ፣ በጠንቋይ፣ በአታላዮችና በሌሎችም ከአላህ ውጪ ባሉ አካላት ጥበቃ መፈለግ ውድቅ መደረጉን እንረዳለን።
  • ይህ ዱዓእ በሀገሩም ይሁን በጉዞ አንድ ስፍራ ላይ ላረፈ ሰው መደንገጉን እንረዳለን።