ሁለት ሰዎች ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ፊት ተሰዳደቡ። የአንደኛቸው ፊት ቀላ፣ አንገቱ ዘንድ ያሉት ደምስሮቹም ተገታተሩ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "እኔ አንዲትን ንግግር አውቃለሁ ይህ የተናደደ ሰው ቃሏን ቢናገራት ቁጣው ከርሱ ይወገድለት ነበር። አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧኒ ረጂም ቢል ይወገድለት ነበር።" ለርሱም "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከሸይጧን በአላህ ተጠበቅ እያሉህ ነው።" አሉት። እርሱም እብደት ያለበት ሰው ካልሆነ በቀር ከሸይጧን የማይጠበቅ መስሎት "እኔ እብድ ነኝ እንዴ?" አላቸው።