ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ወደ ሌላ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ መመልከቱን ወይም ሴት ልጅ ወደ ሌላ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ መመልከቷን ከለከሉ። ሀፍረተ ገላ ማለት: ግልፅ የሆነ ጊዜ የሚያሳፍር የሆነ አካል ሁሉ ነው። የወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ ከእምብርት እስከ ጉልበቱ ሲሆን፤ የሴት ልጅ ደግሞ ከባዕድ ወንዶች አንፃር ሁሉም ሰውነቷ ሀፍረተ ገላ ነው። ከሴቶችና ከዘመዶቿ አንፃር ደግሞ በተለምዶ ቤት ውስጥ ስሰራ ግልፅ የሚሆነውን ያክል ግልፅ ታደርጋለች። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ተራቁቶ ከሌላው ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ ወይም ለብቻቸው ከአንድ ብርድ ልብስ ስር መገለላቸውን ከለከሉ። ሴት ልጅም ተራቁታ ወደ ሴት ልጅ በአንድ ልብስ ውስጥ ወይም ለብቻቸው ከአንድ ብርድ ልብስ ስር መገለላቸውን ከለከሉ። ምክንያቱም ይህ አንዱ የሌላኛው ጓደኛውን ሀፍረተ ገላ ወደመንካት ያደርሰዋልና። መንካቱ ደግሞ እንደማየቱ ክልክል ነው። እንደውም ወደ ትልቅ ብክለት ስለሚያመራ መንካቱ ከማየትም በበለጠ ክልክል ነው።