ሂሻም ቢን ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- ዐረብ ባልሆኑ ገበሬዎች በኩል ሲያልፍ ከፀሐይ ሐሩር በታች እንዲቆሙ ተደርገው ተመለከተ። ስለ ሁኔታቸውም ጠየቀ። ይህ የተደረገባቸው ግብር መክፈል እየቻሉ ባለመክፈላቸው እንደሆነም ተነገረው። ሂሻምም -አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና- ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ እንደሰማው እመሰክራለሁ አለ: አላህ ያለ አግባብ በግፍ በዱንያ ውስጥ ሌሎችን የሚቀጡ ሰዎችን ይቀጣቸዋል።