ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከበደል አስጠነቀቁ። ከበደል መካከልም: ሰዎችን መበደል፣ ነፍስን መበደል፣ በአላህ ሐቅ ላይ በደል መፈፀም ይጠቀሳሉ። በደል ማለት ሁሉንም የሐቅ ባለቤቶችን ሐቃቸውን ከመስጠት መተው ነው። በደል የትንሳኤ ቀን በባለቤቱ ላይ ከሚያጋጥመው መከራዎችና አስፈሪ ክስተቶች አኳያ ጨለማ ነው። ከስስትም ከለከሉ። እርሱም ከመጓጓት (መንሰፍሰፍ) ጋር እጅግ ስስታምነት ነው። ከስስታምነት መካከል: ገንዘባዊ ሐቆችን ከመወጣት ቸል ማለትና ለዱንያ እጅግ መንገብገብም ይጠቀሳል። ይህኛው የበደል ክፍል ማለትም ስስታምነት ከእኛ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷቸዋል። ይህም ከፊሉ ከፊሉን እንዲገድሉና አላህ እርም ያደረጋቸውን ክልክሎች የተፈቀዱ እንዲያደርጉ አነሳስቷቸዋል።