ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በወንጀል፣ በሽርክና ሰዎችን በመብታቸው በመበደል ላይ ከመዘውተር አስጠነቀቁ። ምክንያቱም አላህ በዳይን ያዘገየዋል፣ ያቆየዋል ፣ እድሜውንና ገንዘቡንም ያረዝምለታል። በቅጣትም አያቻኩለውም። ካልቶበተ ግፉ ስለበዛ ይይዘዋል አይለቀውምም አይተወውምም። ቀጥለውም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም {የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው። ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው።} [ሁድ: 102] የሚለውን አነበቡ።