አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል። የአደምን ልጅ ሆድ ከአፈር በቀር የሚሞላው የለም። ወደ አላህ ተፀፅቶ በተመለሰ ሰው ላይም አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል።"» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።