ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፦ "አዋጅ! ዱንያ የተረገመች ናት። አላህን ማውሳት፣ አላህን ከማውሳት ጋር የተቆራኘ፣ ዐዋቂ (ዐሊም) ወይም ዕውቀት ፈላጊ ካልሆነ በቀር በዱንያ ውስጥ ያለውም የተረገመ ነው።" ሐሰን ነው። - ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።