ከዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዓንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "መስካችሁ ላይ ሙጥኝ አትበሉ ዱንያን ትከጅላላችሁና።"» حسن لغيره - ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የአትክልትና የእርሻ (የስራ) መስክ ላይ ሙጥኝ ማለትን ከለከሉ። ይህም ዱንያን ለመከጀልና ከአኺራ ይልቅ ወደ ዱንያ እንዲዘነበል ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከአኺራ የሚያዞር በሆነ መልኩ ዱንያን ሙጥኝ ማለት መከልከሉን እንረዳለን።
  • ሐዲሡ ውስጥ የተከለከለው ለመኖሪያ የሚሆን የገቢ ምንጭ መያዝ አይደለም። የተከለከለው ዱንያ ውስጥ መስመጥና አኺራን መርሳት ነው።
  • ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "በሐዲሡ የተፈለገው: አላህን ከማስታወስ ስለሚያዘናጋችሁ የስራ መስካችሁን በመያዝ አትስመጡ ማለት ነው።"