ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚስቶችን ከመምታት ከለከሉ። የአማኞች አዛዥ ዑመር ቢን አልኸጧብም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሴቶች ባሎቻቸውን ተዳፈሩ። ስነምግባራቸውም ተበላሸ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የባልን ሐቅ አለመወጣት እምቢተኝነትን ማሳየት፣ ባልን ማመፅና የመሳሰሉት ምክንያቶች ከተከሰቱ የማያቆስል ምት እንዲመቷቸው ፈቀዱ። ከዛም በኋላ ባሎቻቸው ይህንን ፍቃድ በመጥፎ መንገድ በመጠቀም የሚያቆስል ምት የመቷቸው ሚስቶች የነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚስቶች ዘንድ ቅሬታ ሊያሰሙ መጡ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: ከናንተ ምርጦቹ እነዚያ ሚስቶቻቸውን የሚያቆስል ምት የሚማቱት ወንዶች አይደሉም።