explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሟቾችን መሳደብና ክብራቸውን መንካት ክልክል መሆኑን አብራሩ። ከእኩይ ስነ ምግባሮችም የሚመደብ እንደሆነ ገለፁ። ምክንያቱም ይህ ስድብ በህይወት ያሉ ሰዎችን ከመጉዳት በዘለለ ለነርሱ የማይደርሳቸው ከመሆኑም በተጨማሪ እነርሱ ወዳስቀደሙት መልካምም ይሁን መጥፎ ስራቸው ደርሰዋልና።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ሐዱሡ ሟቾችን መሳደብ ክልክል መሆኑን ይጠቁማል።
  • ሟቾችን ከመሳደብ መታቀብ የህያው ሰዎችን ጥቅምም የማህበረሰቡንም ሰላም ከመጣላትና ከመናቆር ይጠብቃል።
  • ሟቾችን ከመሳደብ የመከልከሉ ጥበብ ወዳስቀደሙት ስራ ስለደረሱ መስደቡ ከንቱ ስለሆነና በተጨማሪ የህያው ቅርብ ዘመዶቹን ስለሚያውክ ነው።
  • የሰው ልጅ ጥቅም የሌለውን ነገር መናገር አይገባውም።