explain-icon

ትንታኔ

የጠራውና ከፍ ያለው አላህ ከሰዎች ውስጥ ለእውነት እጅ መስጠትን የማይቀበል፣ እውነታውን በክርክሩ ለመመለስ የሚሞክር ወይም እውነትን ይዞ ቢከራከርም ነገር ግን ከሚዛናዊነት በሚያስወጣው መልኩ ክርክርን የሚያበዛና ያለ እውቀት የሚከራከርን ደረቅ ተከራካሪንና ክርክር የሚያበዛን እንደሚጠላ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ተበዳይ ሀቁን ሸሪዓዊ በሆነ መልኩ መክሰሱ የተወገዘ የሆነው የክርክር ይዘት ውስጥ አይገባም።
  • ክርክርና ንትርክ በሙስሊሞች መካከል ልዩነትና ጀርባ መሰጣጠትን ከሚየስከትሉ የምላስ ወለምታዎች ናቸው።
  • እውነትን ይዞና በጥሩ ዘይቤ ከሆነ ክርክር የተወደሰ ይሆናል። ውሸትን ለማፅናትና እውነትን ለመመለስ ከሆነ ወይም ያለማስረጃ ከሆነ ደግሞ የተወገዘ ክርክር ይሆናል።