ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦቻቸውን: ድሀ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን? ብለው ጠየቁ። እነርሱም: በመካከላችን ድሃ የምንለው ገንዘብና እቃ የሌለውን ነው አሉ። እርሳቸውም: በኡመቴ ውስጥ የትንሳኤ ቀን ድሃ የሚባለው እንደ ሶላት፣ ዘካና ፆም የመሰሉ መልካም ስራዎችን ይዞ የሚመጣ ነው። (ነገር ግን) ሲመጣም ይህንን ሰድቦታል፣ ይህንን በክብሩ ዘልፎታል፣ የዚህን ገንዘብ በልቶ ክዶታል፣ የዚህን ደም አፍስሶ በድሎታል፣ ይህንን ደግሞ ደብድቦ አዋርዶታል። ለተበዳዮቹም ከምንዳዎቹ እየተቀነሰ ይሰጣቸዋል። እርሱ ላይ ያሉት ሐቆችና በደሎች ተፈርዶ ሳይጠናቀቅ መልካም ስራው ከተጠናቀቀ ከተበዳዩ ወንጀል ይወሰድና ወደ በዳዩ መዝገብ ይደረጋል። ከዚያም ምንም መልካም ስራ ስላልቀረው እሳት ውስጥ ተወርውሮ ይጣላል።