ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላግባብ እርግማን የሚያበዛ ሰው ለሁለት ቅጣቶች እንደሚዳረግ ተናገሩ: የመጀመሪያው: የትንሳኤ ቀን መልክተኞች ለህዝቦቻቸው ተልእኳቸውን እንዳደረሱ ከሚመሰክሩ ምስክሮች አይሆኑም፤ አመፀኛ ስለሆነም በዱንያም ምስክርነቱ ተቀባይነት አይኖረውም፤ ሰማዕትነትንም እርሱም በአላህ መንገድ መገደል ስለሆነ አይገጠምም። ሁለተኛው: አማኞች የትንሳኤ ቀን እሳት መግባት ግድ የሆነባቸውን ወንድሞቻቸውን በሚያማልዱበት ጊዜ እነርሱ ግን አያማልዱም።