ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የአንድ ሙስሊም እስልምና በተሟላ መልኩ የሚያምረውና ኢማኑ የሚሞላው ከማያገባው፣ ከማይመለከተው፣ ከማይጠቅመውና ከማያሳስበው ንግግርና ተግባር ወይም ከማይመለከተው ዲናዊና ዱንያዊ ጉዳይ ሲርቅ እንደሆነ ገለፁ። አንድ ሰው በማይመለከተው ነገር መጠመዱ ምናልባት ከሚጠቅመው ነገር ያዘናጋዋል ወይም መራቅ የሚገባውን ነገር እንዲፈፅም ይዳርገዋል። የሰው ልጅ የትንሳኤ ቀን ስለስራዎቹ ተጠያቂ ነውና።