የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ከሶፊያ‘ኮ (የፈለገችውም የአማኞች እናትን ነው) ከአካላዊ ነውሮቿ እርሷ አጭር መሆኗ ይበቃሃል።" አለቻቸው። እርሳቸውም "ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል ውሃውን አሸንፋ የምትለውጠውንና የምታበላሸውን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት። እንዲህም አለች "የሆነን ሰው ዝቅ በማድረግ መልኩ የሚሰራውን ስራ አምሳያ አስመስዬ ሰራሁላቸው።" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ነውሩን መናገር ወይም የሚሰራውን ስራ አስመስዬ በመስራቴ ወይም የሚናገረውን አምሳያ በመናገሬ ለዚህ ተግባር ከዱንያ እጅግ በርካታ ነገር ቢሰጠኝ ራሱ ማድረጉ አያስደስተኝም።" አሉ።