ከጃቢር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "ሸይጧን በጀዚረተል ዐረብ (በባህር የተከበበው የዐረብ ምድር) ውስጥ ሰጋጆች ያመልኩኛል የሚለውን ተስፋ ቆርጧል። ነገር ግን በሰጋጆች መካከል ማጣላትን (ተስፋ አልቆረጠም)።"» ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።