ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው በላጩ? ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ሁለት ነገሮችን ጠቀሱ። የመጀመሪያው: ድሃዎችን ማብላትን ማብዛት ነው። እዚህ ውስጥም ሶደቃ፣ ስጦታ፣ ግብዣ፣ የሰርግ ድግስ ይገባሉ። የማብላቱ በላጭነትም በረሃብና ኑሮ በተወደደበት ወቅት የጠነከረ ይሆናል። ሁለተኛው: አወቅከውም አላወቅከውም በሁሉም ሙስሊም ላይ ሰላምታን ማቅረብ ነው።