explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትላልቆቹን ወንጀሎች መጠንቀቅ እንደቅድመ መስፈርት ከተሟላ አምስቱ በቀንና ሌሊት የሚከናወኑት ሶላቶች፣ በየሳምንቱ የሚሰገደው የጁምዐ ሶላትና በየአመቱ የረመዳንን ወር መፆም በመካከላቸው የሚፈፀምን ትናንሽ ወንጀሎችን እንደሚያስምሩ ነገሩን። ዝሙትና መጠጥን የመሰሉ ከባባድ ወንጀሎች በተውባ ካልሆነ በቀር አይሰረዙም።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከወንጀሎች መካከል ከባባድና ትናንሽ የሚባሉ እንዳሉ እንረዳለን።
  • ትናንሽ ወንጀሎች የሚሰረዙት ከባባዶቹን ወንጀሎች መራቅን እንደመስፈርት ማሟላት ከተቻለ መሆኑን እንረዳለን።
  • ትላልቅ ወንጀሎች የሚባሉት ወይ በዱኒያ ቅጣት የተወሰነባቸው፣ ወይም በአኼራ የሚያስከትሉትን የቅጣት አይነት የተነገረባቸው፣ ወይም የአላህ ቁጣ የመጣባቸው፣ ወይም ከባድ ዛቻ ያለባቸው፣ ወይም ደግሞ አድራጊው የተረገመባቸው ሲሆኑ ነው። ለምሳሌ፡ ዝሙት፣ መጠጥ መጠጣት ይጠቀሳሉ።