ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለሙናፊቆችና ሶላትን በጀማዓ መገኘት ላይ በተለይ የዒሻእና ፈጅር ሶላት ላይ ስላላቸው ስንፍና፤ እነርሱ ሁለቱን ሶላት ከሙስሊም ጀመዓ ጋር መስገድ የሚያስገኘውን አጅር እና ምንዳ መጠን ቢያውቁ ኖሮ ህፃን ልጅ በሁለት እጆቹና ጉልበቱ እንደሚዳኸው እንሱም እየዳኹ ይመጡ እንደነበር ተናገሩ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ኢቃም እንድትባል አዘው በሳቸው ምትክ አንድ የሚያሰግድ ሰው ሊመድቡና ከዚያም የታሰረ እንጨት ከተሸከሙ ሰዎች ጋር በመሆን ጀመዓ ሶላት ወደማይገኙ ወንዶች ሂደው ጀመዓ ባለመገኘት የሰሩት ወንጀል ከባድ ስለሆነ ቤታቸውን በእሳት ሊያቃጥሉ ቆርጠው ነበር። ነገር ግን ቤት ውስጥ ንፁህ ሴቶች፣ ህፃናትና ሌሎችም የሚያስቀር ምክንያት ያላቸው ስላሉ አላደረጉትም።