የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የፈጅርን ሶላትና የዐስርን ሶላት የሰገደና በመስገድም የዘወተረ አንድም ሰው (የጀሀነም) እሳት እንደማይገባ ተናገሩ። እነዚህን ሁለት ሶላቶች የለዩት ከባባድ ሶላቶች ስለሆኑ ነው። የሱብሒ ወቅት በጣፋጭ እንቅልፍ ወቅት የሚሰገድ ነው፤ የዐስር ወቅት ደግሞ ሰው በቀን ስራና ንግድ በሚጠመድበት ጊዜ የሚሰገድ ነው። ይህ አይነት ችግር ከመኖሩም ጋር እነዚህን ሁለት ሶላቶች የተጠባበቀ ሰው በተቀሩትም ሶላቶች ላይ መጠባበቁ አይቀርም።