ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የፈጅርን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ጥበቃና ከለላ ስር ስላለ እንደሚከላከልለትና እንደሚረዳው ተናገሩ። ከዚያም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የፈጅርን ሶላት በመተው ወይም ሰጋጁን በመተናኮልና ሰጋጁ ላይ ወሰን በማለፍ ይህንን ከለላ ከማፍረስ አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመም ይህንን ጥበቃ ስለጣሰ ለብርቱ ዛቻ የተጋለጠ ይሆናል። የአላህን ሀቅ ወሰን ስላለፈም በአላህ ይፈለጋል። አላህም የሚፈልገውን ያገኘዋል፤ ከዚያም በአፍጢሙ እሳት ውስጥ ይደፋዋል።