ከጃቢር አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው፦ አንድ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- “ እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና በዛም ላይ ምንም ካልጨመርኩ ጀነት እገባለሁን?” ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና “አዎን!” አሉት። እሱም፦ "በዚህ ላይ አንድንም ላልጨምር በአላህ እምላለሁ! " አለ። ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።