ከሳሊም ቢን አቢ ጀዕድ እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: "አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: 'ምናለ ሰግጄ እረፍት ባገኘሁ።' አለ። ሰዎቹ በዚህ ንግግሩ ላይ ያነወሩት መስሎ ሲታይም እንዲህ አለ: 'የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'" ሶሒሕ ነው። - አቡዳውድ ዘግበውታል።