ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙአዚንን በምንሰማ ጊዜ ለርሱ ጥሪ መልስ በመስጠት ላይ አነሳሱ (አበረታቱ)። ምላሹም በየአንዳንዱ አረፍተ ነገር ሙአዚኑ የሚለውን በማለት ነው። ተክቢራው በሚያደርግ ጊዜ እኛም ከርሱ በኋላ ተክቢራ እናደርጋለን፣ ሁለቱን የምስክር ቃላት (ሸሀደተይንን) በሚል ጊዜ እኛም ከርሱ በኋላ እንላለን፣ (ሐይየ ዐለስ-ሶላህና ሐይየ ዐለል ፈላሕ) የሚሉት ሁለቱ አረፍተ ነገሮች ግን ይለያሉ። ከነርሱ በኃላ የምንለው "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" (ብልሃትም ሆነ ኃይል ከአላህ ውጪ የለም) ነውና።