ከመዕዳን ቢን አቢ ጦልሐ አልየዕመሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ ነፃ ያወጡት ባሪያ የነበረውን ሠውባንን አገኘሁትና እንዲህ አልኩት: አላህ በርሱ ምክንያት ጀነት እንድገባ የሚያደርገኝን የምሰራውን ስራ ንገረኝ? ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ስራ ንገረኝ? እርሱም ዝም አለ። በድጋሚ ጠየቅኩት አሁንም ዝም አለ። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቅኩት እርሱም: "ስለዚህ ጉዳይ የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠየቅኳቸውና እንዲህ አሉኝ ‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›"» መዕዳን እንዲህ አለ «ቀጥሎ አቡ ደርዳእን አገኘሁና ጠየቅኩት። እርሱም ሠውባን ያለኝን አምሳያ ነገረኝ።» ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።