ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስራ ምን እንደሆነ ተጠየቁ። እርሳቸውም "ግዴታ ሶላቶችን አላህ በገደበው ወቅት መስገድ ነው።" ብለው መለሱ። ቀጥሎም በጎ በማድረግ፣ ሐቃቸውን በመጠበቅ፣ ሐቃቸውን ከመጨፍለቅ በመቆጠብ ለወላጆች መልካም መዋል ነው። ቀጥሎም የአላህን ንግግር የበላይ ለማድረግ፣ ከኢስላምና ከተከታዮቹ ጠላቶችን ለመመከትና የኢስላምን ምልክቶች ይፋ ለማድረግ በአላህ መንገድ መታገል ነው። ይህም በነፍስና በገንዘብ ነው። ኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚህን ስራዎች ነገሩኝ። ለርሳቸው 'ከዚያስ ቀጥሎ' ብላቸው ኖሮ ግን ይጨምሩልኝ ነበር።" አሉ።