የአማኞች እናት ዓኢሻ (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) እንዳወሳችው: አንድ ሚስኪን ሴት ሁለት ሴት ልጆቿን ተሸክማ ዓኢሻን ለመነቻት። ዓኢሻም ሶስት ቴምሮችን ሰጠቻት። ለእያንዳንዷ ልጆቿ አንድ አንድ ቴምር ሰጠችና አንዷን ቴምር ደግሞ ልትበላት ወደ አፏ አስጠጋች። ነገር ግን ልትበላት የፈለገቻትን አንዷን ቴምር ሁለቱ ልጆቿ መፈለጋቸውን ተረዳችና ያንኑም ቴምር ለሁለት ከፍላ አከፋፈለቻቸው። የሴትዬዋ ጉዳይም ዓኢሻን (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) ስለደነቃት ሴትዬዋ የሰራችውን ሁሉ ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገረቻቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሏት: "አላህ በዚህች ተምር ምክንያት ወይ ጀነትን ግድ አድርጎላታል፤ ወይም ደሞ በዚህች ተምር ምክንያት ከእሳት ነፃ አድርጓታል።